Amharic




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን፡፡

በአፋን ኦሮሞ ወልዳ ዱካ ቡኦታ ማለት ማኅበረ ሐዋሪያት ማለት ሲሆን ሲጀመር ማህበረ ነህምያ ተብሎ ሲጠራ የነበረዉ የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ደንብ፤ስርዓት እና  አስተምህሮን መሰረት በማድረግ በኦሮምኛ ቋንቋ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ነዉ፡፡ የማህበሩ ዋና ዓላማም ትምህርተ-ኃይማኖትን፤ወንጌልን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማዳረስ ቤተ ክርስቲያናችን በምታደርገዉ እንቅስቃሴ ሁሉ ከአባቶች ጎን በመቆም በሚችለዉ ሁሉ የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከት ነዉ፡፡በተለይ በአሁኑ ሰዓት ቋንቋን እንደ ትልቅ መሳሪያነትም በመጠቀም ብዙዎች መንጋዎችዋን በመንጠቅ ላይ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ የሆነ ሁሉ  የሃይማኖቱን ትክክለኛነት፤ጥንታዊነት እና ቤተ-ክርስቲያናችንም ሐዋሪያዊት መሆንዋን አዉቆ በሃይማኖቱ እንዲጸና እንዲበረታ ማድረግ፤ ነዉ፡፡ ይህም ዓላማ ይሳካ ዘንድ መጻህፍት እዲተረጎሙ፤በቋንቋዉ የሚያገለግሉ መምህራን እዲበራከቱ፤የአገልጋዮች እጥረት በከፍተኛ ደረጃ በሚታይባቸዉ ቦታዎች የአግልግሎት መረሃ ግብር በማዘጋጀት የእምነቱን ተከታይ እንዲማር ማትጋት ነዉ፡፡
ማህበሩ የተቋቋመዉ በወርኃ ጥቅምት፣2004 ዓ.ም ሲሆን ከግንቦት 2004 ዓ፣ም ጀምሮ በትምህርተ ሃማኖት ላይ ብቻ በማተኮር መንፈሳዊ ጽሑፎችን በየሁለት ሳምነቱ በተከታታይ በዚህ ብሎግ ሳይት ላይ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፤አሁንም እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ወደፊት በስፋት መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ይሰራል፡፡ እርሶም ይህን ሀሳብ ይደግፋል፤ ይረዳል፤ ያሳድጋል  በሚሉት ሁሉ ይሳተፉ፤ ይደግፉ፡፡ አስተያየትዎን በ waldaa2004@gmail.com  ያድርሱን፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር፤ወለወላዲቱ ድንግል፤ ወለመስቃሉ ክቡር፡፡

No comments:

Post a Comment

Note: Only a member of this blog may post a comment.